Addis Capital

          (  0111262411 / 0111263514           *: 54782                          Fax : 0111262445                                                                                             Email : addiscapital@addiscapital.com.et                                                                  

ለለውጥ የሚሰራ ሞዴል የካፒታል ዕቃ ኪራይ አጋርዎ 

Select Language

ዜናዎች

 

 

የጠቅላላ ጉባኤ አባላቱ መደበኛ ስብሰባ አደረጉg

የጠቅላላ ጉባዔው አባላቱ በትናትናው ዕለት ኩባኒያው ባስገነባው አዲስ ህንጻ ላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ባተኮሩ አራት አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጽድቋል፡፡

ጉባዔው በተለይም የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ በሆኑት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራ አባይ ባቀረቡት የ2017 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን በማድመጥ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ማወቅ ተችሏል፡፡

በቀረበው ሪፖርት ላይ የጠቅላላ ጉባዔው አባል የሆኑት አቶ አዋሽ እንደገለጹት ከሆነ ተቋቋሙ ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ መሆኑንና ይህን መሰረት አድርጎ ደንበኞችን ለማርካት ከተደራሽነትም  ሆነ ከአገልግሎት አንጻር በቀጣይ ብዙ ስለሚጠበቅበት ለመስራት ስትራተጂ አስቀምጦ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይም ትኩረት አድርጎ ሊሰራ ይገነባል፡፡

‘’የኩባኒያው የብድርና የኪራይ አመላለስ ጥሩ አፈጻጸም ላይ ነው’’ ያሉት የጠቅላላ ጉባዔው አባል የሆኑት አቶ አባተ ስጦታው የደንበኞች እርካታን በማወቅ ይበልጥ አገልግሎትን ለማሻሻል ዳሰሳ መደረግ አለበት፤ ከ IT ሲስተምም ጋር ተያይዞ ጊዜ ተወስዶ መሰራት እንዳለበት ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡

የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የ ኩባኒያው የጠቅላላ ጉባኤው አባል የሆኑ አቶ አብዱልቃድር በበኩላቸው ‘’ኩባኒያው በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ይህን ህንጻ ገንብቶ እዚህ ደረጃ ላይ ማድረሱና የፋይናንስ ዕጥረት ኖሮበትም ኢንተርፕራይዞችን በማስጠቀም በዚህ ቁመና መዝለቁ የሚበረታታ ነው’’ ብለዋል፡፡

የጠቅላላ ጌባዔ አባላቱ ባነስዋቸው የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ እና የኩባኒያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሳይ እንሴኔ ምላሾችን ሰጥተዋል፡፡

የጠቅላላ ጉባዔው አባላት የ2017 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፓርትና የውጭ ኦዲተር ሪፓርት በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

ኩባኒያው የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ገመገመ፤

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. በተከታታይ ለ አምስት ቀናት የኩባኒያው ማኔጅመንት አባላትን እና ቅ/ስ/አስኪያጆችን ባካተተ የ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን በማድረግ የቀጣይ 6 ወራት መተግበር ያለባቸውን አበይት አቅጣጫዎችን አስቀምጥዋል፡፡


ኩባኒያው በተያዘው በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸሙ ለኢንተርፕራይዞች በተለያዩ ዘርፎች የካፒታል ዕቃዎችን በማስተላለፍ ተጠቃሚ ለከማድረግ ባለፈ ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎችም ስራ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መልካም አጋጣሚን መፍጥ መቻሉን ተገልጽዋል፡፡


የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና ውይይትን አስመልክቶ የኩባኒያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መሳይ እንሴኔ እንደገለጹት ከሆነ አሁን ላይ እንደተደረገው የግምገማ እና ውይይት ሂደት ቀጣይነት የሚኖረው ሆኖ ቅርንጫፎችም ክፍተቶችን በማረም ጥንካሬዎቻቸውን በማጎልበት የተሸለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ዕቅዳቸውን በመከለስ በፍጥነት ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
በወቅቱ በ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ እና ውይይት ላይ ተሳታፊ የነበሩት የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች በበኩላቸው በቀሪ ወራቶች ከምንጊዜውም በላቀ መናበብ በመድረኩ የተሰጡ ገንቢ ሃሳቦችን ስንቅ በማድረግ ለተፈጻሚነቱ ተግተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

 የኩባንያው ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መስፍን አበራ በበኩላቸው ‘’በ ቀጣይ ቀሪ ወራቶች ጠንክረን መስራት አለብን’’ ሲሉ ፤ የአስተዳደር ዘርፍ ም/ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተገኝ ጦፋ በበኩላቸው ‘’ስራው ይበልጥ በእውቀት ተመርቶ ውጤታማ እንዲሆን ስልጠናዎች ይሰጣሉ’’ ብለዋል፡፡
‘’ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በቀሪ 6 ወራት ውስጥ ዕቅዳቸውን ከልሰው ከማሳካት ጎን ለጎን የሶፍት ዌር ሲስተም ትግበራንም አጠናክራችሁ በመቀጠል የኩባንያውን አፈጻጸም በጋራ በመሆን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ‘’በማለት የኩባኒያው ማ/ዳይሬክተር አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ኩባንያው በባለፉት 10 የኦፕሬሽናል አገልጎሎት ዓመታት ውስጥ 12,251 አባላት ላሏቸው 5,761 ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች 26,265 የካፒታል ዕቃዎችን በብር 2,318,705,916 በማስተላለፍ ለ 24,471 በከተማችን ለሚገኙ ስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድልን በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ 

 ኩባንያው 17ኛውን ጠቅላላ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ፤
የህንጻ ግንባታውም  ያለበት ደረጃ ተጎበኘ፤

የአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል የጠቅላላ ጉባዔ አባላት በተገኙበት 17ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በማካሄድ በቀረበው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የኦዲት ሪፖርት ላይ በመወያየት አጸደቀ፡፡የጠቅላላ ጉባዔው ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር ም/ከንቲባ እና የጠቅላላ ጉባዔው ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጃንጥራር ዓባይ የ2016 በጀት ዓመት ፋይናንሽያል እና ኦፕሬሽናል ሪፖርቶችን ለጠቅላላ ጉባዔ አባላት በማቅረብ መድረኩ ለውይይት ክፍት እንዲሆን አድርገው የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

የቀረበውን ሪፖርት መሠረት አድርገው የጠቅላላ ጉባዔ አባል የሆኑት አቶ አዋሽ አብተው እንደገለጹት ከሆነ ሪፖርቱ ተቋሙ ከቆመለት ዓላማ አንጻር ጥሩ ስራ እየተሰራ መሆኑን ያመለካተ እና የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸሙም እንዳመላከተው ውጪ ያለ ገንዘብ ማደጉን ያሳየ ነው፡፡
‘’የብድር አመላለስ ላይም ተስፋ ሰጪና የሚበረታታ ነው’’ በማለት ከሪፖሰስ ጋር ተያይዞ ግን ‘’ለምን?’’ ተብሎ ጥያቄ በማንሳት በየፈርጁ በመተንተን ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን አቶ አዋሽ አክለዋል፡፡
‘’ሪፖርቱ በዋናነት ወደ ሀብቱ፣ ህንጻው (አሴት) እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ ማድላቱ አበረታች ነው’’ ያሉት አቶ አብዱ ከሀብት ማፈላለግ ጋር ተያይዞ ከአክስዮን ባለፈ አማራጮችን ወይም ልምዶችን ማየት ቢቻል መልካም መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የጠቅላላ ጉባዔ አባላቱ ባነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ አስተያየቶቹ ተቋሙን የሚገነቡት በመሆኑ ተቀባይነት እንዳላቸው በመግለጽ የትርፍ ምንጭ ቀድሞ ከዋናው የስራ መስክ ያልነበረ ሲሆን የዘንድሮው ትርፍ ግን ከተቋቋመበት ከዋናው ስራ የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

ክቡር ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው የተነሱ አስተያየቶች ገንቢ መሆናቸውን አስገንዝበው በቀጣይ በሪፖርቱ ላይ ሆነው እንዲካተቱ አስገንዝበዋል፡፡
በሌላ በኩል የኩባንያው ህንጻ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ የጎበኘው ጠቅላላ ጉባዔው በተቋራጭ ድርጅቱ ገለጻ የተሰጠው ሲሆን፣ ገለጻውን በመንተራስ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በተቋራጭ ድርጅቱ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በዋነኝነት ግን እንደ ክቡር ም/ከንቲባ ከሆነ ‘’ተቋራጩ በፊት ባሳየው ፍጥነት ልክ ዓለመቀጠሉ እንደ ድክመት ታይቶ ስራውን ሳያቋርጥ የፋይናንስ ችግርን ተቋቁሞ የመንግስት ተቋም መሆኑን በመረዳት ስራው ሊጓተት አይገባም ነብር’’ ብለዋል፡፡

‘’አሁን ላይ ህንጻዎች በሁለት ወራት ውስጥ ተገንብተው እየተጠናቀቁ ነው ‘’ያሉት ክቡር ከንቲባው ኩባንያው አሁን ላይ በኪራይ እየተቸገረ በመሆኑ በቶሎ በሚቀጥሉት ሁለት እና ሶስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት መዋል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

 

ከታች የዞረ

ኩባኒያው የ2017 በጀት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያየ፤ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ሰራተኞችም ዕውቅና ሰጠ፤

አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ትናንት የኩባኒያው አመራሮችና መላው ሰራተኛ በተገኘበት በ2017 በጀት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አደረገ፡፡

 የውይይት መድረኩን ይመሩት የነበሩት የኩባኒያው ኮር አመራሮች በ2017 በጀት የዕቅድ አፈጻጸም  ሪፖርት  ግምገማና  የ2018  በጀት ዓመት  ዕቅድ  ላይ  የቀረቡ ጥያቄና  አስተያየቶችን  ተከትሎ  የተለያዩ  ምላሾች  ሰጥተዋል፡፡

የቀረበውን ሪፖርትና ዕቅድን ተከትሎ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ እስከዳር ጥላሁን እንደገለጹት ከሆነ ከ2017 መወሰድ ያለበትን ተሞክሮ በመውሰድና ድክመትን በማረም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ ልንተጋ ይገባል፡፡

ኩባኒያው ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ በበኩላቸው ‘’በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ሰኔ ወር ሲደረግ የነበረውን ርብርብ እንደተሞክሮ በመውሰድ በ2018 በጀት ዓመት የጸደቀውን እቅድ ለማሳካት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል’’ ብለዋል፡፡

የኩባኒያው ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መስፍን አበራ እንደገለጹት ከሆነ የ2018 ዕቅድን በመረባረብ የተሰጠውን ዕቅድ ማሳካት ከቻለ ኩባኒው ትርፋማ በማድረግ ለሰራተኛው ከበፊቱ በተሸለ ሁኔታ በተነሳሽነት መስራት አለበት፡፡

የኩባኒያው ዋና ስራ አስፈጻሚ በዕለቱ በሰራተኛው ዘንድ የተነሳሽነት ስሜት ይበልጥ መፈጠር እንዳለበት አጽንኦት በመስጠት ጥሩ የተሸለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ሰራተኞች እውቅና በመስጠት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የ‘’ IFARS’’ ሰልጠና ተሳታፊዎችን

ኩባንያው ብቁ የሰው ኃይልን ከማፍራት አንጻር እየሄደባቸው ካሉ እርቀቶች መካከል ከላይ የተመላከቱት የ ‘’ IFARS’’ ሰልጠና ተሳታፊዎችን መመልከቱ ሁነቱን ያስረዳል፡፡ ሰልጣኞቹ ወቅቱን የዋጀውን ይህን የስልጠና ዘርፍ ለ10 ተከታታይ ቀናት  በመውሰድ ዕውቀት ቀስመው የኩባንያውን የፋይናንስ ሰራና የመረጃ አሰናነድን ወደላቀ ደረጃ ያደርሱታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኩባንያው ዕውቅና ተሰጠው

አዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል በኢንደስትሪ ቢሮ አዘጋጅነት ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016ን አፈጻጸም እና 2017 በጀት ዓመት ዕቅድን መሰረት አድርጎ ከ25 በላይ የሆኑ ባለድርሻ አካላት በተሳተፋበት ኩባንያው ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ የሆኑት ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ ካፒታልን አስመልክቶ እንደገለጹት ከሆነ ኩባንያ ለኢንደስትሪው ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ነው፡፡


ኩባንያው ማ/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዞች በመስሪያ ቦታ ችግር እና በግባት አቅርቦት እየተቸገሩ በመሆኑ መፍትሄ መሰጠት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በወቅቱ በሪፖርቱ እና ዕቅዱ ላይ ውይይት ከማድረግ ባለፈ ቀጣይ አቅጣጫዎችን መሠረት ያደረገ አብሮ የመስራት የትስስር ሰነድ ፍርርምም ተካሂዷል፡፡


በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባዔው የጠቅላላ ጉባዔው የቀረበውን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የኦዲት ሪፖርትን ካደመጠ በኋላ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ታውቋል፡፡
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. ከ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ2016 በጀት ዓመት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገቡን ማሳያዎች አመላክተዋል።

የግንዛቤ መድረኩ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ 

በጉለሌ ክ/ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በክ/ከተማው መሰብሰቢያ አዳራሽ የባለድርሻ አካላትን ባካተተ መልኩ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቁጥራቸው ከ 3መቶ በላይ ለሆኑ ለአዲስ እና ነባር ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደተቻለ ተገልጽዋል፡፡


‘’በውይይት መድረኩ ላይ ከተሰብሳቢ አዲስ እና ነባር ኢንተርፕራይዞች የኪራይ እና ወለድ ልዩነት፣የብድር ጣሪያንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄ እና አስተያየቶች ቀርበው ፖሊሲውን መሰረት ያደረገ ምላሽ ተሰጥቷል ‘’ ያሉት አቶ ይስሃቅ በቀጣይም በተለይ በማንፋክቸሪንግ ዘርፍ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን አክለዋል፡፡

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ ለ 1መቶ13 ኢንትፕራይዞች 33ሚሊየን ብር የሚያወጡ የተለያዩ የካፒታል ዕቃዎችን ከማስጠቀም ባለፈ በአፈጻጸሙም የ2ኛ ደረጃን በመያዝ እውቅና እንደተቸረው ይታወሳል፡፡

ከታች የዞረ

„እንዴት በቅንጅት ወጣቶች እና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል“ በሚለው ውይይት  ተካሄደ

 በኢትዮጵያ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ማህበር አስተባባሪነት የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ኩባንያዎች፣ ማይክሮ ፋይናንሶች እና ለወጣቶች እና ሴቶች ላይ የሚሠሩ ግብረ ሰናይ ድርጀቶች በቅንጅት እንዴት በቅንጅት ወጣቶች እና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል በሚለው በዛሬው ዕለት በጌትፋም ሆቴል ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

እየተካሄደ ያለውን ውይይት ዓላማ አስመልክቶ ከSMEFP ወ/ሮ የመንዝ ወርቅ እንደገለፁት ከሆነ የማይክሮ ፋይናንስ እና የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ ተቋማት ተቀናጅተው መሥራት ለወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድልን ከመፍጠር አኳያ ጉልህ ሚናን ይጫወታሉ ።
ወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ ተቋማት ፣ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተቀናጅተው ለመሥራት መድረኩ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን አመላክተዋል ።

መድረኩ ለውይይት ይበልጥ ክፍት ይሆን ዘንድ ሬይ እና ኮሜርሽያል ፓል የዲጂታል ብድር እና አሰራራቸውን አስመልክቶ ገለፃ ሲያደርጉ ‚impact evaluation report for the parent smef“ በሚል በሊዝ ካፒታል ተጠቃሚዎች ላይ የተካሄደ ጥናት በዶክተር አበበ አምባቸው ቀርቦ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል ።
የኢትዮጵያ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ማህበር ከተመሠረተበት 2014 ጀምሮ እየሠራቸው ካሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች አንዱ በዛሬው እለት ተለያዩ ትስስሮችን በመፍጠር ስልጠና እና የዕውቀት ልምዶችን ማዘጋጀት መሆኑን ልብ ይሏል ።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ

በአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ከ 60 በላይ ከሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ የ ስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ባለሙያዎች በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳሪያ ሊዝ ዘገልግሎት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ በወረዳ 5 ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደ የውይይት መድረክ በኩባንያው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን ታውቋል፡፡


የስብሰባውን ዓላማ አስመልክቶ የቅርንጫፋ ስራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ደበበ እንደገለጹት ከሆነ በክ/ከተማው ስር ላሉ በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳርያ ሊዝ ድጋፍ እንዴት እና ከየት ማግኘት እንደሚችሉ የሚያስረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መፍጠርን ያለመ ነው፡፡

የውይይት ተሳታፊዎች በቀጣይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ92 ኢንተርፕራይዝ 802 የካፒታል ዕቃ በብር 52,484,212.03 በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡

የውይይት ተሳታፊዎች በቀጣይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ92 ኢንተርፕራይዝ 802 የካፒታል ዕቃ በብር 52,484,212.03 በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ 

በየካ ክ/ከተማ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት በትናንትናው ዕለት በምስራቅ አጠቃላይ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኩባንያውን አገልግሎትን አስመልክተው በስፍራው ለነበሩ ከ1መቶ 70 በላይ ለሆኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ላሉ አምራች ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ መስጠታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

 በአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ የ ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ከ 50 በላይ በክ/ከተማው የኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ፣ የሚመለከታቸው የስራ እና ክህሎት ባለሙያዎች ፣ የሚመለከታቸው አካላት፣ በጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት በ ክ/ከተማው ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በክ/ከተማው መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ በኩባንያው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን ከቅርንጫፋ ጽ/ቤት ማወቅ ተችሏል፡፡

የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ዓላማን አስመልክተው የቅርንጫፋ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሲሳይ ጌታቸው እንደገለጹት ከሆነ ለአምራች ኢንደስትሪዎች ስለ ማሽነሪ ብድር አቅርቦት፣ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ፓኬጅና የዘርፋ ማኅበራት አደረጃጀትን አስመልክቶ የተዘጋጀ የስልጠና እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደነበር በመግለጽ በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳርያ ሊዝ አገልግሎት እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል፡፡ 

እንደ አቶ ሲሳይ ገለጻ ከሆነ በውይይት መድረኩ ላይ በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን የመስሪያ ቦታ ኪራይ ውል ዓመት መብዛቱንና መሰል ጥቄዎችና አስተያየቶች በመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተው ምላሽ እንደሰጡባቸው ገልጸዋል፡፡

ከታች የዞረ

የውይይት ተሳታፊዎች የኩባንያው ብሎም የቅርንጫፋ አገልግሎት አሰጣጥ ተስፋ ሰጪ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጋር አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ68 ኢንተርፕራይዝ በብር 88,433,529 የሚያወጡ 337 የካፒታል ዕቃ በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡

የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ሊዝ ትስስር 

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ 

በየካ ክ/ከተማ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት በትናንትናው ዕለት በምስራቅ አጠቃላይ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኩባንያውን አገልግሎትን አስመልክተው በስፍራው ለነበሩ ከ1መቶ 70 በላይ ለሆኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ላሉ አምራች ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ መስጠታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

በአዲስ ካፒታል የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስቻለው ወርቁ የተካሄደውን የውይይት መድረክ ዓለማን አስመልክተው እንደገለጹት ከሆነ ኢንተርፕራይዞች በአጠቃላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይነት በአሰራር እና ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ በተለይም ከካፒታል ዕቃዎች አንጻር፣ ከግብዓት አቅርቦትና ከፋይናንስ አንጻር በምን መልኩ መሰራት እንዳለበት ያለመ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

በተዘጋጀው የውይይጥ መድረክ ላይ የመድረክ ተሳታፊዎች የካፒታል ዕቃ ተጠቃሚነት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የብድር ጣሪያው ለምን ከፍ አይልም፣ራሳችን ለምን አናስመጣም፣ የወለድ ምጣኔው በዝቷል የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተንጸባረቀው በስራ አስኪያጁ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ ተቋማቱ በጋራ ዕቅድ በማቀድ ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው እና ታች ድረስ በመውረድ ለኢንተርፕራይዞች አገልግሎት በመስጠት ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት እንደተሰጠውም ማወቅ ተችሏል፡፡
የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ እንዳመላከተው ለ79 ኢንተርፕራይዞች በብር 72.4 ሚሊየን የካፒታል ዕቃዎችን ማስጠቀሙ ይታወቃል፡፡

የካፒታል እቃ ፋይናንስ ሊዝ ትስስር ስዕላዊ መግለጫ

.