Addis Capital
( 0111262411 / 0111263514 *: 54782 Fax : 0111262445 Email : addiscapital@addiscapital.com.et
ለለውጥ የሚሰራ ሞዴል የካፒታል ዕቃ ኪራይ አጋርዎ
Select Language
l
አቶ መሳይ እንሴኔ የአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈፃሚ
እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፣ በሊዝ ፋይናንሱ ዘርፍ የካፒታል ዕቃዎችን ዕውቀቱ፣ ክህሎቱና ሙያው ኖራቸው በፋይናንስ ዕጥረት መስራት ላልቻሉ በጥቃቅን፣አነስተኛና መካከለኛ ለተደራጁ የከተማችን ነዋሪዎች እንደ ኩባንያ ተጠቃሚ ማድረግ በመቻላችን ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ኩባንያችን በተለያዩ ዘርፎች አዳዲስ የሊዝ ፋይናንስ መፍትሄዎችን በማቅረብ ለኢንተርፕራይዞች የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻሉ የኩባንያው አመራሮች እና ሰራተኞችን በመምራቴም እንዲሁ ደስታ ይሰማኛል። ተልዕኳችን ፡- የገንዘብ ፍሰትን በመጠበቅ የስራ ቅልጥፍናን የሚያሻሽሉ የሊዝ ፋይናንስ አማራጮችን በማቅረብ ኩባንያችንን ማበረታታት ነው።
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ፣ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተነደፉ ለተለያዩ ዘርፎች አገልግሎት የሚውሉ የካፒታል ዕቃዎችን በሊዝ ያስጠቅማል። ስራዎን ለማስፋፋትም ሆነ ለመጀመር እየፈለጉ ከሆነ፣ በትንሽ ቅድመ ክፍያ ሸክሞን በመጋራት ዘመናዊ መሣሪያዎችን እንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡
ደንበኞቻችን በአጋርነታችን አስደናቂ እድገት አሳይተዋል። አሁን ላይ የኩባንያችንን አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን በከፍተኛ ደረጃ የተለወጡ ኢንተርፕራይዞችን ብንቃኝ የእኛን የተበጀ የሊዝ ፋይናንስ መፍትሄዎችን ከተጠቀሙ በኋላ የማምረት አቅማቸውን በተሳካ ሁኔታ መጨመሩን ያመላክታችኋል፤ የኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ማደግ፤ ለስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድልን ከመፍጠር አኳያም እንዲሁ የተሻለ መደላድልን መፍጠራቸው ዋቢ ይሆናችኋል፡፡ኩባንያው ከስራው በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታን ከመወጣት አንጻርም በተለየ ሁኔታ ለሴቶች፣ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች የካፒታል ዕቃ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር በመፍጠር እና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
በ2030 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ ‘’ሞዴል የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ተቋም’’ ለመሆን እና እየሰጠው ያለውን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሰለጠነ የሰው ኃይል በማጎልበት በሊዝ ፋይናንስ ዘርፍ የሚታየውን ውድድር በማሸነፍ ፣እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት በሚፈለገው ደረጃ ለማርካትና አዳዲስ የቢዝነስ ሐሳቦችን በማመንጨት ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋፅኦ ለማድረግ የሠራተኛው፣ የአመራሩ በቁርጠኝነትና በቅንጅት መንቀሳቀስ እንዳለብን እያስገነዘብኩ የደንበኞቻችን ትብብርና የባለድርሻ አካላት እገዛ ከጎናችን እንደሚሆን ፅኑ እምነት አለኝ፡፡
.
የማሽን ብድር፡ ለስራ ፈጣሪዎች ምን ያህል አቅም እየሆናቸው ነው?