( 0111262411 / 0111263514 *: 54782 Fax : 0111262445 Email : addiscapital@addiscapital.com.et
ለለውጥ የሚሰራ ሞዴል የካፒታል ዕቃ ኪራይ አጋርዎ
Select Language
ዜናዎች
የኩባንያው ሰራተኞችና የፕሮሰስ ካውንስል አባላት የህንጻ ጉብኝት አካሄዱ፤
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ አስገንብቶ ወደስራ የገባበትን አዲሱ ህንጻ ሰራተኞቹንና የፕሮሰስ ካውንስሉን አስጎበኘ፡፡
በወቅቱ ህንጻውን የጎበኙ አንዳንድ የኩባንያው ሰራተኞች እንገለጹት ከሆነ ይህ ህንጻ የራዕያችን መገለጫ እና የቀጣይ ህልማችን መተግበሪያ ተምሳሌት ጭምር ነው ብለዋል፡፡
የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መሳይ እንሴኔ በበኩላቸው ‘’ለህንጻ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የሰራተኛው እና የህንጻ ተቋራጩ ያለመታከት ባደረጉት ጥረት ነውና ሊመሰገኑ ይገባል’’ ብለዋል፡፡
የአትዮጵያ የሊዝ ፋይናነስ ማህበር ስራ አሲያጅ የሆኑት አቶ አስፋው በበኩለቸው ‘’አዲስ ካፒታል ከሀገራችን ባለፈ በምስራቅ አፍሪካም ጭምር በሞዴልነት በሌሎች የሊዝ ፋይናንስ ተቋማት እየተወሰደ ያለ ለመሆኑ ማሳያ አሁን ላይ የአፍሪካ አገራት ሳይቀር ለልምድ ቅመራ ጉብኝት ተመረጭ እያደረጉት ነው ብለዋል፡፡
ኩባንያው በቀጣይ በጀት ዓመት ከምንጊዜውም በላቀ ተደራሽነትና አገልግሎት ዜጎችን የካፒታል እቃ ተጠቃሚ ለማድረግ ከወዲሁ የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ኩባኒያው አዲስ ባስገነባው ህንጻ ላይ የበጀት ዓመቱን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ገመገመ፤
አዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ‘’የበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም የቱን ያክል ተደራሽ በመሆን ለከተማችን ነዋሪዎች የካፒታል ዕቃ ተጠቃሚ አድርጓል? የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድስ ምንን አካቷል?’’ በሚል የዳይሬክተሮች ቦርድ ግምገማውን አዲስ በተገነባው የኩባንያው ህንጻ ላይ አድርጓል፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ በወቅቱ የዕቅድ አፈጻጸሙን እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በመገምገም የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሸራሸር በበጀት ዓመቱ በብር ከ713 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ከ3 ሺ2 መቶ45 በላይ የካፒታል ዕቃዎች በማስተላለፍ ለ4ሺ ሰባ ስድስት ስራ – አጥ ዜጎች የስራ ዕድልን ከመፍጠር ባለፈ በ2018 በጀት ዓመት ተደራሽነቱን ማስፋትና አገልግሎቱን ማሳለጥ እንዳለበት በክቡር ም/ከንቲባና የቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት አቶ ጃንጥራር አባይ አጽንዖት ተሰጥቷል፡፡
የቦርድ አባለቱ ከሪፖርትና ዕቅድ ግምገማ ውይይት ባለፈ ሕንጻው የደረሰበትን ደረጃንም ጎብኝተዋል፡፡
ኩባንያው እውቅና ተሰጠው
አዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል በኢንደስትሪ ቢሮ አዘጋጅነት ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016ን አፈጻጸም እና 2017 በጀት ዓመት ዕቅድን መሰረት አድርጎ ከ25 በላይ የሆኑ ባለድርሻ አካላት በተሳተፋበት ኩባንያው ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ የሆኑት ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ ካፒታልን አስመልክቶ እንደገለጹት ከሆነ ኩባንያ ለኢንደስትሪው ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ነው፡፡
አዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል በኢንደስትሪ ቢሮ አዘጋጅነት ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016ን አፈጻጸም እና 2017 በጀት ዓመት ዕቅድን መሰረት አድርጎ ከ25 በላይ የሆኑ ባለድርሻ አካላት በተሳተፋበት ኩባንያው ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ የሆኑት ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ ካፒታልን አስመልክቶ እንደገለጹት ከሆነ ኩባንያ ለኢንደስትሪው ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ነው፡፡
በነፋስ ስልክ ክ/ከተማ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ውይይት ተካሄደ ።
በቀን 13/06/2017
የኢንዱሥትሪ ልማት ቤት አምራች ኢንዱሥትሪዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተደረገ ሢሆን በዚህም አዲሥ ካፒታል ከመነሻቸዉ ጀምሮ ኢንተርፕራይዞችን ሢደገፋ የቆየ እና በግማሽ አመቱም ያለዉ አፊጻጸም የተሻለ መሆኑን የሚገልጹ አሥተያየቶች የቀረቡ ቢሆንም እንደ ኩባንያ ከዚህ በላይ ማሥጠቀም የምንችልበት አቅም እና በጀት ያለ በመሆኑ ሁሉም አምራች ኢንዱሥትሪዎች ወሥነዉ እንዲጠቀሙ ገላፃ ተደርጓል።
በሌላ መልኩ የማሽነሪ ሊዝ ተጠቃሚ አምራቾች ወርሃዊ ክፋያቸዉን በአግባቡ መከፈል እንዳለበቸዉ ማሣሠቢያ ተሠጧል።
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመፍታት ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ተገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በሁሉም ዘርፍ ተደራጅተው ከሚሰሩ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች እና አንቀሳቃሾች ጋር የሚያጋጥሟቸውን ማነቆች ለመለየትና ለመፍታት እንዲያስችል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
ተደራጅተው ስራ ላይ ባሉ ኢንተርፕራይዞች ላይ የሚታዩ ማነቆዎች ዙሪያ ባለ ድርሻ አካላት ባሉበት በቦሌ ክ/ከተማ የውይይት መድረክ ተዘጋጀ.።
ኩባንያው ማ/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዞች በመስሪያ ቦታ ችግር እና በግባት አቅርቦት እየተቸገሩ በመሆኑ መፍትሄ መሰጠት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በወቅቱ በሪፖርቱ እና ዕቅዱ ላይ ውይይት ከማድረግ ባለፈ ቀጣይ አቅጣጫዎችን መሠረት ያደረገ አብሮ የመስራት የትስስር ሰነድ ፍርርምም ተካሂዷል፡፡
ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመፍታት ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ተገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በሁሉም ዘርፍ ተደራጅተው ከሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች እና አንቀሳቃሾች ጋር የሚያጋጥሟቸውን ማነቆች ለመለየትና ለመፍታት እንዲያስችል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከስኬት ባንክና ከአዲስ ካፒታል የመሳሪያ ዕቃ አስመጪ አ.ማ ጋር በጋራ በመሆን ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት
የመድረኩ ላይ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደተናገሩት የመድረኩ ዋና ዓላማ ኢንተርፕራይዞችየሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በጋራ በመፍታት በቀጣይ ለሚሰሩት ስራ አቅም ከዚህ በፊት የተሰሩ ተሞክሮችን በማድረግ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዋነኝነት በስራ ውስጥ ላሉ ፣ ወደ ስራ እየገቡ ያሉ እንዲሁም ስራ ውስጥ ሆነው ከግንዛቤ ማነስ ውጤታማ ላልሆኑ ኢንተርፕራይዞች ወደ ውጤታማነታቸውን መጨመር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡13/06/2017
„እንዴት በቅንጅት ወጣቶች እና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል“ በሚለው ውይይት ተካሄደ
በኢትዮጵያ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ማህበር አስተባባሪነት የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ኩባንያዎች፣ ማይክሮ ፋይናንሶች እና ለወጣቶች እና ሴቶች ላይ የሚሠሩ ግብረ ሰናይ ድርጀቶች በቅንጅት እንዴት በቅንጅት ወጣቶች እና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል በሚለው በዛሬው ዕለት በጌትፋም ሆቴል ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።
እየተካሄደ ያለውን ውይይት ዓላማ አስመልክቶ ከSMEFP ወ/ሮ የመንዝ ወርቅ እንደገለፁት ከሆነ የማይክሮ ፋይናንስ እና የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ ተቋማት ተቀናጅተው መሥራት ለወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድልን ከመፍጠር አኳያ ጉልህ ሚናን ይጫወታሉ ::
ወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ ተቋማት ፣ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተቀናጅተው ለመሥራት መድረኩ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን አመላክተዋል ።
መድረኩ ለውይይት ይበልጥ ክፍት ይሆን ዘንድ ሬይ እና ኮሜርሽያል ፓል የዲጂታል ብድር እና አሰራራቸውን አስመልክቶ ገለፃ ሲያደርጉ ‚impact evaluation report for the parent smef“ በሚል በሊዝ ካፒታል ተጠቃሚዎች ላይ የተካሄደ ጥናት በዶክተር አበበ አምባቸው ቀርቦ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል ።
የኢትዮጵያ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ማህበር ከተመሠረተበት 2014 ጀምሮ እየሠራቸው ካሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች አንዱ በዛሬው እለት ተለያዩ ትስስሮችን በመፍጠር ስልጠና እና የዕውቀት ልምዶችን ማዘጋጀት መሆኑን ልብ ይሏል ።
የየካ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ቤት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ያለመ የጋራ የምክክር መድረክ ተዘጋጀ::
የካቲት 14/2017 ዓ.ም የካ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ኮሙኒኬሽን
ፅህፈት ቤቱ ከክፍለ ከተማው መስሪያ ቦታዎች አስተዳደር፣ ከስኬት ባንክ እና ከአዲስ ካፒታል ጋር በመተባበር የአምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት እና ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚያስችል የጋራ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል።
የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት በኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) እንደገለፁት እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ሪፎርም በተከታታይ ሲሰራ መቆየቱን አንስተው ብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ታምርት በሚል መሪ ቃል ኢንዱስትሪውን የበለጠ ለማነቃቃት ንቅናቄ እየተካሄደ እንደሚገኝ እና የዛሬውም መድረክ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር ሱራፌል እሸቴ በበኩላቸው መድረኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን መሰረታዊ ማነቆዎች ችግሮች በመለየት ምላሽ ለመስጠት በማለም መዘጋጀቱን አንስተው አምራቾች ከመስሪያ ቦታ፣ ከብድር እና ከመስሪያ ማሽን ጋር በተያያዘ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በፍጥነት በመፍታት ምርትና ምርታማነትን በይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች በየዘርፋቸው ያጋጠማቸውን ችግሮች በዝርዝር አቅርበው የሚመለከታቸው ተቋማት ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ
በአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ከ 60 በላይ ከሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ የ ስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ባለሙያዎች በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳሪያ ሊዝ ዘገልግሎት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ በወረዳ 5 ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደ የውይይት መድረክ በኩባንያው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን ታውቋል፡፡
የስብሰባውን ዓላማ አስመልክቶ የቅርንጫፋ ስራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ደበበ እንደገለጹት ከሆነ በክ/ከተማው ስር ላሉ በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳርያ ሊዝ ድጋፍ እንዴት እና ከየት ማግኘት እንደሚችሉ የሚያስረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መፍጠርን ያለመ ነው፡፡
የውይይት ተሳታፊዎች በቀጣይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ92 ኢንተርፕራይዝ 802 የካፒታል ዕቃ በብር 52,484,212.03 በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡
የውይይት ተሳታፊዎች በቀጣይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ92 ኢንተርፕራይዝ 802 የካፒታል ዕቃ በብር 52,484,212.03 በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከስኬት ባንክና ከአዲስ ካፒታል የመሳሪያ ዕቃ አስመጪ አ.ማ ጋር በጋራ በመሆን ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት
የመድረኩ ላይ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠረት በለጠ እንደተናገሩት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በጋራ በመፍታት በቀጣይ ለሚሰሩት ስራ አቅም ከዚህ በፊት የተሰሩ ተሞክሮችን በማድረግ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተዘጋጀው የውይይጥ መድረክ ላይ የመድረክ ተሳታፊዎች የካፒታል ዕቃ ተጠቃሚነት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የብድር ጣሪያው ለምን ከፍ አይልም፣ራሳችን ለምን አናስመጣም፣ የወለድ ምጣኔው በዝቷል የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተንጸባረቀው በስራ አስኪያጁ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ ተቋማቱ በጋራ ዕቅድ በማቀድ ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው እና ታች ድረስ በመውረድ ለኢንተርፕራይዞች አገልግሎት በመስጠት ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት እንደተሰጠውም ማወቅ ተችሏል፡፡
የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ እንዳመላከተው ለ79 ኢንተርፕራይዞች በብር 72.4 ሚሊየን የካፒታል ዕቃዎችን ማስጠቀሙ ይታወቃል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ
በአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ የ ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ከ 50 በላይ በክ/ከተማው የኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ፣ የሚመለከታቸው የስራ እና ክህሎት ባለሙያዎች ፣ የሚመለከታቸው አካላት፣ በጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት በ ክ/ከተማው ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በክ/ከተማው መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ በኩባንያው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን ከቅርንጫፋ ጽ/ቤት ማወቅ ተችሏል፡፡
የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ዓላማን አስመልክተው የቅርንጫፋ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሲሳይ ጌታቸው እንደገለጹት ከሆነ ለአምራች ኢንደስትሪዎች ስለ ማሽነሪ ብድር አቅርቦት፣ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ፓኬጅና የዘርፋ ማኅበራት አደረጃጀትን አስመልክቶ የተዘጋጀ የስልጠና እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደነበር በመግለጽ በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳርያ ሊዝ አገልግሎት እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል፡፡
.
እንደ አቶ ሲሳይ ገለጻ ከሆነ በውይይት መድረኩ ላይ በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን የመስሪያ ቦታ ኪራይ ውል ዓመት መብዛቱንና መሰል ጥቄዎችና አስተያየቶች በመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተው ምላሽ እንደሰጡባቸው ገልጸዋል፡፡
የውይይት ተሳታፊዎች የኩባንያው ብሎም የቅርንጫፋ አገልግሎት አሰጣጥ ተስፋ ሰጪ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጋር አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ68 ኢንተርፕራይዝ በብር 88,433,529 የሚያወጡ 337 የካፒታል ዕቃ በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡
የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ሊዝ ትስስር
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ
በየካ ክ/ከተማ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት በትናንትናው ዕለት በምስራቅ አጠቃላይ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኩባንያውን አገልግሎትን አስመልክተው በስፍራው ለነበሩ ከ1መቶ 70 በላይ ለሆኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ላሉ አምራች ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ መስጠታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ
በየካ ክ/ከተማ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት በትናንትናው ዕለት በምስራቅ አጠቃላይ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኩባንያውን አገልግሎትን አስመልክተው በስፍራው ለነበሩ ከ1መቶ 70 በላይ ለሆኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ላሉ አምራች ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ መስጠታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡
በአዲስ ካፒታል የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስቻለው ወርቁ የተካሄደውን የውይይት መድረክ ዓለማን አስመልክተው እንደገለጹት ከሆነ ኢንተርፕራይዞች በአጠቃላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይነት በአሰራር እና ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ በተለይም ከካፒታል ዕቃዎች አንጻር፣ ከግብዓት አቅርቦትና ከፋይናንስ አንጻር በምን መልኩ መሰራት እንዳለበት ያለመ መሆኑን ተመላክቷል፡፡