Addis Capital

          (  0111262411 / 0111263514           *: 54782                          Fax : 0111262445                                                                                             Email : addiscapital@addiscapital.com.et                                                                  

ለለውጥ የሚሰራ ሞዴል የካፒታል ዕቃ ኪራይ አጋርዎ 

Select Language

ዜናዎች

 

 

ኩባኒያው የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ገመገመ፤

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. በተከታታይ ለ አምስት ቀናት የኩባኒያው ማኔጅመንት አባላትን እና ቅ/ስ/አስኪያጆችን ባካተተ የ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን በማድረግ የቀጣይ 6 ወራት መተግበር ያለባቸውን አበይት አቅጣጫዎችን አስቀምጥዋል፡፡


ኩባኒያው በተያዘው በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸሙ ለኢንተርፕራይዞች በተለያዩ ዘርፎች የካፒታል ዕቃዎችን በማስተላለፍ ተጠቃሚ ለከማድረግ ባለፈ ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎችም ስራ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መልካም አጋጣሚን መፍጥ መቻሉን ተገልጽዋል፡፡


የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና ውይይትን አስመልክቶ የኩባኒያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መሳይ እንሴኔ እንደገለጹት ከሆነ አሁን ላይ እንደተደረገው የግምገማ እና ውይይት ሂደት ቀጣይነት የሚኖረው ሆኖ ቅርንጫፎችም ክፍተቶችን በማረም ጥንካሬዎቻቸውን በማጎልበት የተሸለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ዕቅዳቸውን በመከለስ በፍጥነት ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
በወቅቱ በ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ እና ውይይት ላይ ተሳታፊ የነበሩት የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች በበኩላቸው በቀሪ ወራቶች ከምንጊዜውም በላቀ መናበብ በመድረኩ የተሰጡ ገንቢ ሃሳቦችን ስንቅ በማድረግ ለተፈጻሚነቱ ተግተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

 የኩባንያው ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መስፍን አበራ በበኩላቸው ‘’በ ቀጣይ ቀሪ ወራቶች ጠንክረን መስራት አለብን’’ ሲሉ ፤ የአስተዳደር ዘርፍ ም/ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተገኝ ጦፋ በበኩላቸው ‘’ስራው ይበልጥ በእውቀት ተመርቶ ውጤታማ እንዲሆን ስልጠናዎች ይሰጣሉ’’ ብለዋል፡፡
‘’ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በቀሪ 6 ወራት ውስጥ ዕቅዳቸውን ከልሰው ከማሳካት ጎን ለጎን የሶፍት ዌር ሲስተም ትግበራንም አጠናክራችሁ በመቀጠል የኩባንያውን አፈጻጸም በጋራ በመሆን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ‘’በማለት የኩባኒያው ማ/ዳይሬክተር አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ኩባንያው በባለፉት 10 የኦፕሬሽናል አገልጎሎት ዓመታት ውስጥ 12,251 አባላት ላሏቸው 5,761 ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች 26,265 የካፒታል ዕቃዎችን በብር 2,318,705,916 በማስተላለፍ ለ 24,471 በከተማችን ለሚገኙ ስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድልን በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ 

 ኩባንያው 17ኛውን ጠቅላላ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ፤
የህንጻ ግንባታውም  ያለበት ደረጃ ተጎበኘ፤

የአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል የጠቅላላ ጉባዔ አባላት በተገኙበት 17ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በማካሄድ በቀረበው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የኦዲት ሪፖርት ላይ በመወያየት አጸደቀ፡፡የጠቅላላ ጉባዔው ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር ም/ከንቲባ እና የጠቅላላ ጉባዔው ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጃንጥራር ዓባይ የ2016 በጀት ዓመት ፋይናንሽያል እና ኦፕሬሽናል ሪፖርቶችን ለጠቅላላ ጉባዔ አባላት በማቅረብ መድረኩ ለውይይት ክፍት እንዲሆን አድርገው የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

የቀረበውን ሪፖርት መሠረት አድርገው የጠቅላላ ጉባዔ አባል የሆኑት አቶ አዋሽ አብተው እንደገለጹት ከሆነ ሪፖርቱ ተቋሙ ከቆመለት ዓላማ አንጻር ጥሩ ስራ እየተሰራ መሆኑን ያመለካተ እና የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸሙም እንዳመላከተው ውጪ ያለ ገንዘብ ማደጉን ያሳየ ነው፡፡
‘’የብድር አመላለስ ላይም ተስፋ ሰጪና የሚበረታታ ነው’’ በማለት ከሪፖሰስ ጋር ተያይዞ ግን ‘’ለምን?’’ ተብሎ ጥያቄ በማንሳት በየፈርጁ በመተንተን ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን አቶ አዋሽ አክለዋል፡፡
‘’ሪፖርቱ በዋናነት ወደ ሀብቱ፣ ህንጻው (አሴት) እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ ማድላቱ አበረታች ነው’’ ያሉት አቶ አብዱ ከሀብት ማፈላለግ ጋር ተያይዞ ከአክስዮን ባለፈ አማራጮችን ወይም ልምዶችን ማየት ቢቻል መልካም መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የጠቅላላ ጉባዔ አባላቱ ባነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ አስተያየቶቹ ተቋሙን የሚገነቡት በመሆኑ ተቀባይነት እንዳላቸው በመግለጽ የትርፍ ምንጭ ቀድሞ ከዋናው የስራ መስክ ያልነበረ ሲሆን የዘንድሮው ትርፍ ግን ከተቋቋመበት ከዋናው ስራ የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

ክቡር ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው የተነሱ አስተያየቶች ገንቢ መሆናቸውን አስገንዝበው በቀጣይ በሪፖርቱ ላይ ሆነው እንዲካተቱ አስገንዝበዋል፡፡
በሌላ በኩል የኩባንያው ህንጻ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ የጎበኘው ጠቅላላ ጉባዔው በተቋራጭ ድርጅቱ ገለጻ የተሰጠው ሲሆን፣ ገለጻውን በመንተራስ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በተቋራጭ ድርጅቱ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በዋነኝነት ግን እንደ ክቡር ም/ከንቲባ ከሆነ ‘’ተቋራጩ በፊት ባሳየው ፍጥነት ልክ ዓለመቀጠሉ እንደ ድክመት ታይቶ ስራውን ሳያቋርጥ የፋይናንስ ችግርን ተቋቁሞ የመንግስት ተቋም መሆኑን በመረዳት ስራው ሊጓተት አይገባም ነብር’’ ብለዋል፡፡

‘’አሁን ላይ ህንጻዎች በሁለት ወራት ውስጥ ተገንብተው እየተጠናቀቁ ነው ‘’ያሉት ክቡር ከንቲባው ኩባንያው አሁን ላይ በኪራይ እየተቸገረ በመሆኑ በቶሎ በሚቀጥሉት ሁለት እና ሶስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት መዋል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባዔው የጠቅላላ ጉባዔው የቀረበውን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የኦዲት ሪፖርትን ካደመጠ በኋላ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ታውቋል፡፡
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. ከ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ2016 በጀት ዓመት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገቡን ማሳያዎች አመላክተዋል።

ኩባንያው ዕውቅና ተሰጠው

አዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል በኢንደስትሪ ቢሮ አዘጋጅነት ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016ን አፈጻጸም እና 2017 በጀት ዓመት ዕቅድን መሰረት አድርጎ ከ25 በላይ የሆኑ ባለድርሻ አካላት በተሳተፋበት ኩባንያው ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡

አዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል በኢንደስትሪ ቢሮ አዘጋጅነት ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016ን አፈጻጸም እና 2017 በጀት ዓመት ዕቅድን መሰረት አድርጎ ከ25 በላይ የሆኑ ባለድርሻ አካላት በተሳተፋበት ኩባንያው ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ የሆኑት ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ ካፒታልን አስመልክቶ እንደገለጹት ከሆነ ኩባንያ ለኢንደስትሪው ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ነው፡፡

ከታች የዞረ


ኩባንያው ማ/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ እንሴኔ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዞች በመስሪያ ቦታ ችግር እና በግባት አቅርቦት እየተቸገሩ በመሆኑ መፍትሄ መሰጠት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በወቅቱ በሪፖርቱ እና ዕቅዱ ላይ ውይይት ከማድረግ ባለፈ ቀጣይ አቅጣጫዎችን መሠረት ያደረገ አብሮ የመስራት የትስስር ሰነድ ፍርርምም ተካሂዷል፡፡

ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመፍታት ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ተገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በሁሉም ዘርፍ ተደራጅተው ከሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች እና አንቀሳቃሾች ጋር የሚያጋጥሟቸውን ማነቆች ለመለየትና ለመፍታት እንዲያስችል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከስኬት ባንክና ከአዲስ ካፒታል የመሳሪያ ዕቃ አስመጪ አ.ማ ጋር በጋራ በመሆን ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት

የመድረኩ ላይ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደተናገሩት የመድረኩ ዋና ዓላማ ኢንተርፕራይዞችየሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በጋራ በመፍታት በቀጣይ ለሚሰሩት ስራ አቅም ከዚህ በፊት የተሰሩ ተሞክሮችን በማድረግ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዋነኝነት በስራ ውስጥ ላሉ ፣ ወደ ስራ እየገቡ ያሉ እንዲሁም ስራ ውስጥ ሆነው ከግንዛቤ ማነስ ውጤታማ ላልሆኑ ኢንተርፕራይዞች ወደ ውጤታማነታቸውን መጨመር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡13/06/2017

„እንዴት በቅንጅት ወጣቶች እና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል“ በሚለው ውይይት  ተካሄደ

 በኢትዮጵያ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ማህበር አስተባባሪነት የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ኩባንያዎች፣ ማይክሮ ፋይናንሶች እና ለወጣቶች እና ሴቶች ላይ የሚሠሩ ግብረ ሰናይ ድርጀቶች በቅንጅት እንዴት በቅንጅት ወጣቶች እና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል በሚለው በዛሬው ዕለት በጌትፋም ሆቴል ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

እየተካሄደ ያለውን ውይይት ዓላማ አስመልክቶ ከSMEFP ወ/ሮ የመንዝ ወርቅ እንደገለፁት ከሆነ የማይክሮ ፋይናንስ እና የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ ተቋማት ተቀናጅተው መሥራት ለወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድልን ከመፍጠር አኳያ ጉልህ ሚናን ይጫወታሉ ::

ወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ ተቋማት ፣ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተቀናጅተው ለመሥራት መድረኩ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን አመላክተዋል ።

መድረኩ ለውይይት ይበልጥ ክፍት ይሆን ዘንድ ሬይ እና ኮሜርሽያል ፓል የዲጂታል ብድር እና አሰራራቸውን አስመልክቶ ገለፃ ሲያደርጉ ‚impact evaluation report for the parent smef“ በሚል በሊዝ ካፒታል ተጠቃሚዎች ላይ የተካሄደ ጥናት በዶክተር አበበ አምባቸው ቀርቦ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል ።
የኢትዮጵያ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ማህበር ከተመሠረተበት 2014 ጀምሮ እየሠራቸው ካሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች አንዱ በዛሬው እለት ተለያዩ ትስስሮችን በመፍጠር ስልጠና እና የዕውቀት ልምዶችን ማዘጋጀት መሆኑን ልብ ይሏል ።

ተደራጅተው ስራ ላይ ባሉ ኢንተርፕራይዞች ላይ የሚታዩ ማነቆዎች ዙሪያ ባለ ድርሻ አካላት ባሉበት በቦሌ ክ/ከተማ የውይይት መድረክ ተዘጋጀ.።

በነፋስ ስልክ ክ/ከተማ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ውይይት ተካሄደ ።

በቀን 13/06/2017

የኢንዱሥትሪ ልማት ቤት አምራች ኢንዱሥትሪዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተደረገ ሢሆን በዚህም አዲሥ ካፒታል ከመነሻቸዉ ጀምሮ ኢንተርፕራይዞችን ሢደገፋ የቆየ እና በግማሽ አመቱም ያለዉ አፊጻጸም የተሻለ መሆኑን የሚገልጹ አሥተያየቶች የቀረቡ ቢሆንም እንደ ኩባንያ ከዚህ በላይ ማሥጠቀም የምንችልበት አቅም እና በጀት ያለ በመሆኑ ሁሉም አምራች ኢንዱሥትሪዎች ወሥነዉ እንዲጠቀሙ ገላፃ ተደርጓል።


በሌላ መልኩ የማሽነሪ ሊዝ ተጠቃሚ አምራቾች ወርሃዊ ክፋያቸዉን በአግባቡ መከፈል እንዳለበቸዉ ማሣሠቢያ ተሠጧል።

የየካ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ቤት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ያለመ የጋራ የምክክር መድረክ ተዘጋጀ::

የካቲት 14/2017 ዓ.ም የካ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ኮሙኒኬሽን

ፅህፈት ቤቱ ከክፍለ ከተማው መስሪያ ቦታዎች አስተዳደር፣ ከስኬት ባንክ እና ከአዲስ ካፒታል ጋር በመተባበር የአምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት እና ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚያስችል የጋራ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል።

የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት በኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) እንደገለፁት እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ሪፎርም በተከታታይ ሲሰራ መቆየቱን አንስተው ብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ታምርት በሚል መሪ ቃል ኢንዱስትሪውን የበለጠ ለማነቃቃት ንቅናቄ እየተካሄደ እንደሚገኝ እና የዛሬውም መድረክ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር ሱራፌል እሸቴ በበኩላቸው መድረኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን መሰረታዊ ማነቆዎች ችግሮች በመለየት ምላሽ ለመስጠት በማለም መዘጋጀቱን አንስተው አምራቾች ከመስሪያ ቦታ፣ ከብድር እና ከመስሪያ ማሽን ጋር በተያያዘ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በፍጥነት በመፍታት ምርትና ምርታማነትን በይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች በየዘርፋቸው ያጋጠማቸውን ችግሮች በዝርዝር አቅርበው የሚመለከታቸው ተቋማት ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

 

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ

በአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ከ 60 በላይ ከሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ የ ስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ባለሙያዎች በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳሪያ ሊዝ ዘገልግሎት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ በወረዳ 5 ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደ የውይይት መድረክ በኩባንያው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን ታውቋል፡፡


የስብሰባውን ዓላማ አስመልክቶ የቅርንጫፋ ስራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ደበበ እንደገለጹት ከሆነ በክ/ከተማው ስር ላሉ በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳርያ ሊዝ ድጋፍ እንዴት እና ከየት ማግኘት እንደሚችሉ የሚያስረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መፍጠርን ያለመ ነው፡፡

የውይይት ተሳታፊዎች በቀጣይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ92 ኢንተርፕራይዝ 802 የካፒታል ዕቃ በብር 52,484,212.03 በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡

የውይይት ተሳታፊዎች በቀጣይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ92 ኢንተርፕራይዝ 802 የካፒታል ዕቃ በብር 52,484,212.03 በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡

በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመፍታት ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ተገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በሁሉም ዘርፍ ተደራጅተው ከሚሰሩ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች እና አንቀሳቃሾች ጋር የሚያጋጥሟቸውን ማነቆች ለመለየትና ለመፍታት እንዲያስችል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከስኬት ባንክና ከአዲስ ካፒታል የመሳሪያ ዕቃ አስመጪ አ.ማ ጋር በጋራ በመሆን ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት

የመድረኩ ላይ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠረት በለጠ እንደተናገሩት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በጋራ በመፍታት በቀጣይ ለሚሰሩት ስራ አቅም ከዚህ በፊት የተሰሩ ተሞክሮችን በማድረግ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ

 በአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ የ ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ከ 50 በላይ በክ/ከተማው የኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ፣ የሚመለከታቸው የስራ እና ክህሎት ባለሙያዎች ፣ የሚመለከታቸው አካላት፣ በጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት በ ክ/ከተማው ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በክ/ከተማው መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ በኩባንያው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን ከቅርንጫፋ ጽ/ቤት ማወቅ ተችሏል፡፡

የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ዓላማን አስመልክተው የቅርንጫፋ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሲሳይ ጌታቸው እንደገለጹት ከሆነ ለአምራች ኢንደስትሪዎች ስለ ማሽነሪ ብድር አቅርቦት፣ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ፓኬጅና የዘርፋ ማኅበራት አደረጃጀትን አስመልክቶ የተዘጋጀ የስልጠና እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደነበር በመግለጽ በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ አባለት የመሳርያ ሊዝ አገልግሎት እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል፡፡ 

.

እንደ አቶ ሲሳይ ገለጻ ከሆነ በውይይት መድረኩ ላይ በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን የመስሪያ ቦታ ኪራይ ውል ዓመት መብዛቱንና መሰል ጥቄዎችና አስተያየቶች በመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተው ምላሽ እንደሰጡባቸው ገልጸዋል፡፡

የውይይት ተሳታፊዎች የኩባንያው ብሎም የቅርንጫፋ አገልግሎት አሰጣጥ ተስፋ ሰጪ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጋር አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት ለ68 ኢንተርፕራይዝ በብር 88,433,529 የሚያወጡ 337 የካፒታል ዕቃ በማስተላለፍ ማስጠቀሙ ይታወሳል፡፡

የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ሊዝ ትስስር 

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ 

በየካ ክ/ከተማ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት በትናንትናው ዕለት በምስራቅ አጠቃላይ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኩባንያውን አገልግሎትን አስመልክተው በስፍራው ለነበሩ ከ1መቶ 70 በላይ ለሆኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ላሉ አምራች ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ መስጠታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግንዛቤን አስጨበጠ 

በየካ ክ/ከተማ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት በትናንትናው ዕለት በምስራቅ አጠቃላይ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኩባንያውን አገልግሎትን አስመልክተው በስፍራው ለነበሩ ከ1መቶ 70 በላይ ለሆኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ላሉ አምራች ኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ መስጠታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

በአዲስ ካፒታል የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስቻለው ወርቁ የተካሄደውን የውይይት መድረክ ዓለማን አስመልክተው እንደገለጹት ከሆነ ኢንተርፕራይዞች በአጠቃላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይነት በአሰራር እና ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ በተለይም ከካፒታል ዕቃዎች አንጻር፣ ከግብዓት አቅርቦትና ከፋይናንስ አንጻር በምን መልኩ መሰራት እንዳለበት ያለመ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

በተዘጋጀው የውይይጥ መድረክ ላይ የመድረክ ተሳታፊዎች የካፒታል ዕቃ ተጠቃሚነት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የብድር ጣሪያው ለምን ከፍ አይልም፣ራሳችን ለምን አናስመጣም፣ የወለድ ምጣኔው በዝቷል የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተንጸባረቀው በስራ አስኪያጁ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ ተቋማቱ በጋራ ዕቅድ በማቀድ ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው እና ታች ድረስ በመውረድ ለኢንተርፕራይዞች አገልግሎት በመስጠት ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት እንደተሰጠውም ማወቅ ተችሏል፡፡
የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ እንዳመላከተው ለ79 ኢንተርፕራይዞች በብር 72.4 ሚሊየን የካፒታል ዕቃዎችን ማስጠቀሙ ይታወቃል፡፡

የካፒታል እቃ ፋይናንስ ሊዝ ትስስር ስዕላዊ መግለጫ