Addis Capital

          (  0111262411 / 0111263514           *: 54782                          Fax : 0111262445                                                                                             Email : addiscapital@addiscapital.com.et                                                                  

ለለውጥ የሚሰራ ሞዴል የካፒታል ዕቃ ኪራይ አጋርዎ 

Select Language

            .   

  1. አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ      ንግድ ስራ  አ.ማ ማን   ነው?

 

4.አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ዋና ዋና መመዘኛ መስፈርቶች

 

5.የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገለግሎት አሰራር ስርዓቶች

 

2. ኩባንያው የሚሰጣቸው      አገልግሎቶች ምንና  ምን  ናቸው?

 

3.   ዕቃ ራይ  ማለት ምን ማለት ነው?

 

 

 

 

አዲስ የካፒታል ዕቃ  ፋይናንስ ንግድ ስራ  አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከሌሎች የከተማው  የልማት ተቋማት ጋር  በመሆን  በ2006  ዓ.ም   የተቋቋመ ነው፡፡ 

በዋናነት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍለ ለተሰሩና ለሚሰማሩ የጥቃቅን፣አነስተኛና መካከለኛ የኢንተርፕራይዞች የማምረቻ መሳሪያዎችን ገዝቶ በማቅረብ የመሳሪያ ሊዝ አገልግሎት የመስጠትና

ኩባንያው በአሁን ሰዓት ለሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በየክፍለ ከተሞች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በመክፈት አገለግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

                                               

    • የዱቤ ግዥ(Hire purchase) 
    • የፋይናንንሽያል ኪራይ(Financial leasing) 
    • የምክር አገልግሎት(Consultancy service)                 መስጠት ናቸው፡፡

 

የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ማለት በፋይናንስ ኪራይ ወይም በዱቤ ግዢ ኪራይ ዘዴዎች መለዋወጫን ጨምሮ ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የካፒታል እቃዎች ፋይናንስ አቅርቦት ስርዓት ነው፡፡.

 

 

 

    • አዋጭ፣ ህጋዊ የንግድ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ
    • በአግባቡ ተሞልቶ በሁሉም ገጾች የኢ/ይዙ ማህተም የሚያርፍበት ከኩባንያው የሚቀርብ ቢዝነስ ፕላን እና የማሽን መጠየቂያ ቅጽ
    • እንዲገዙላቸው የሚፈልጓቸው ማሽኖች ዝርዝር (specification)
    • የመሳሪያው ዋጋ 15 በመቶ ወይም በላይ ቅድሚያ ለመክፈል የተዘጋጀ
    • የተጠየቁት ማሽኖች ለመትከል በቂና መሰረተ ልማቱ የተሟላ ቦታ
    • የመስሪያ ቦታው የመንግስት ሼድ ከሆነ የኪራይ ውል/የግል ቦታ ከሆነ የካርታ ኮፒ/ከሌላ ግለሰብ የኪራይ ቦታ ከሆነ በውልና ማስረጃ የጸደቀ የኪራይ ውል ኮፒ፣
    • የኢንተርፕራይዙ የጥ/አነስተኛ/ታዳጊ መካከለኛ የእድገት ደረጃ ኮፒ
    • ቲን፣ የንግድ ምዝገባ ኮፒ (የንግድ ስራ ፈቃድ ከነጀርባው 2 ኮፒ)፣
    • የኢ/ይዙ አባላት የአ/አበባ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ፣ የሥራ አስኪያጅ 2 ጉርድ ፎቶ
    • የግል ኢንተርፕራይዝ ወይም ፒኤልሲ ከሆነ የአባላት የጋብቻ ሰርቲፊኬት ወይም ያላገባ ማስረጃ ኮፒ
    • ማህበር ከሆነ የመመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ 2 ኮፒ.
    • የኢ/ይዙ አባላት በሙያው የሰለጠኑበት (ሲኦሲ) ወይም ከታወቀ ማምረቻ ድርጅት የሙያ ልምድ ማስረጃ ኮፒ
    • የብድር ታሪክ ደብዳቤ ከወረዳቸው የአዲስ ብድርና ቁ.ተቋም ማቅረብ
    • በመንግስት ሼድ ከሆኑ ከክ/ከተማ የመስሪያ ቦታ ልማትና አስ. ጽ/ቤት ወይም ከአነ/መካ/ማኑ/ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ውልና የማሽን ይሰጣቸው ድጋፍ ደብዳቤ
    • በአግባቡ ተሞልቶ በሁሉም ገጾች የኢ/ይዙ ማህተም የሚያርፍበት ከኩባንያው የሚቀርብ ቢዝነስ ፕላን እና የማሽን መጠየቂያ ቅጽ

 

 

 

    • ከውጭ አገር የሚገቡ ምርቶችን ለሚተኩ (Import Substitution) እና ወደ ውጭ አገር ለሚላኩ (Export Goods) ምርቶችን ለሚያመረቱ፣በክላስተርማዕከላት በመሰባሰብና በመስራትላይላሉ ንተርፕራይዞች፣መስፈርቱን ለሚያሟሉሴቶች፣ልዩድጋፍ የሚያሰፈልጋቸው ክፍሎች፣ለቴክኒክና ሙያ እና ለዩነቨርሲቲ ምሩቃን ወጣቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡
    • በጨርቃጨርቅናአልባሳት፣ቆዳ፣ረታብረት፣እንጨት፣የምግብ ዝግጅት፣የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ምርት፣የዕደ-ጥበብ ውጤቶች፣ኮንስትራክሽን ግብዓት ምርቶች፣አግሮ ፕሮሰሲንግ፣በመልሶ መጠቀምና ሌሎች የማምረቻ የስራ መስኮች የተጠቃሚዎችን ጥያቄ መሰረት በማድረግ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
    • ከኢንተርፕራይዞች ምንም ዓይነት ዋስትና(ማስያዣ) ሳይጠየቅ የማምረቻ መሳሪያውን ዋጋ 15-35% ብቻ በመክፈልና15(35) በመቶ የባለቤትነት መብት በማያዝ መሳሪያውን ወስደው መጠቀም ያስችላል፣
    • የመሳሪያ ኪራይ ዋጋ ክፍያ ተመን በዓመታዊ ተቀናሽ ስሌት annual declining ሆኖ በዓመት ከ14-15 በመቶ ነው፣
    • ስራ ሁኔታን(የቢዝነሱን)አዋጭነት ከግምት ውስጥ በማስገቨባት የመሳሪያው ኪራይ ክፍያ ማጠናቀቂያ የቆይታ ጊዜ ከ 3-8 ዓመታት ነው፣
    • ኩባንያው ለአንድ ኢንተርፕራይዝ እሰከ 10,000,000 ብር(አስር ሚሊዮን ብር) የሚያወጡ የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ ያቀርባል፣
    • ከኮሚሽኒንግ በኋላ ለአዲስ ቢዝነስ ማኑፋክቸሪንግ እስከ 6 ወራት፣ ለነባር ኢንተርፕራይዝ ደግሞ እሰከ 4 ወር የሚደርስ የእፎይታ ጊዜ(gracing period) ይሰጣል፡፡

 6.የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት መጠቀም የሚያስገኛቸው ጥቅሞች ምን ምን ናቸው?

    • አገልግሎትን ያለ ምንም የዋስትና መያዣ ማግኘት መቻሉ፣
    • የሚቀርቡ ማምረቻ መሳሪያዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ መደረጋቸው፣
    • በየወሩ አነስተኛ ክፍያ በመፈፀም የማሽን ባለቤት መሆን ማስቻሉ፣
    • ተከራይ የካፒታል ዕቓውን በኪራይ በማግኘቱ ያለውን ካፒታል ለስራ ማስኬጃ የሚያውለው ስለሆነ ለካፒታል ቁጠባ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ፣
    • የተከራዮችን የንግድ እንቅስቃሴ፣የመክፈል አቅም ሁኔታና ፍላጎት መሰረት ያደረገ የክፍያ መጠንና የክፍያ ጊዜ ስምምነት ማድረግ የሚያስችል መሆኑ፣
    • እንደ ጥሬ ገንዘብ ለሌላ ላልተፈለገ ዓላማ የማይውል መሆኑ፣
    • ተከራዩ የጥሬ ገንዘብ ፍሰቱን በዕቅድ እንዲመራ ማስቻሉ፣
    • ከ4-6 ወር የሚደርስ የብድር መክፈያ እፎይታ ጊዜ መስጠቱ እና ሌሎች ጥቅሞችን ያስገኛል፣