( 0111262411 / 0111263514 * 54782 Fax : 0111262445 Email : addiscapital@addiscapital.com.et
Addis Capital Goods Finance Business S.co
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ን.ስ አ.ማ
Select Language









l
አቶ ጃንጥራር አባይ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ
በዓለም ላይ የሊዝ አገልግሎት መጠን በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱ ይታወቃል (የዓለም የሊዝ አገልግሎት 2019 በእ.ኤ.አ(ፈረንጆች አቆጣጠር) በታተመ የሊዝ መፅሀፍ) እንደ ሚያሳየው በአማካይ 8 ፐርሰንት በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱና ከሪል እስቴት ውጪ ሌሎች (ፋይናንሻል ፣ ኦፕሬቲንግ እና የዱቤ ግዥ) ፋይናንስ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እየበረከቱ(እየበዙ) ይገኛሉ፡፡
በአፍሪካ ከሚገዙ እቃዎች በሊዝ የሚገዙት ሲታይ 1 ፐርሰንት ብቻ ሲሆን በሌላው ዓለም ግን ከ20 እስከ 40 ፐርሰንት በመሆኑ በአሁጉራችን አፍሪካ እና በአፍሪካ ቀንድ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የአለም ሊዝ መፅሀፍ 2019 በእ.ኤ.አ የተደረገ ጥናት ያሳያል እና በአፍሪካ መንግስታት ዓመታት ድጋፍ እና ትኩረት ተሰጥቶት እዳልነበረ ያሳያል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣዉ የአስር ዓመት ስትራተጂክ እቅድ መሰረት በ2030 እ.ኤ.አ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ መንግስት በሁሉም ዘርፍ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል የኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማረጋገጥ መንግስት ካወጣቸዉ ዋና ዋና አላማዎች መካከከል አንዱ የተመቻቸ ሁኔታ በመፍጠር ሁሉም ዜጋ የንብረት ባለቤት እንዲሆን በማድረግ የእድገቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እና መንግስት የማህበራዊ አገልግሎት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ሁሉም ዜጋ የእድገቱ ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል፡፡
የግንባታው በስኬታማነት መጠናቀቅ የከተማው አስተዳደር ቃል ኪዳኖችን ወደ ተግባር ለመተርጎም እና ለነዋሪዎች ተጨባጭ ውጤቶችን ለማምጣት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ሆኖ ተገልጧል።
ከፍተኛ ጥራት ያለው መዋቅር የከተማው ዋና ዋና የልማት ተነሳሽነቶችን ለመከተል ባደረገው ጥረት ቁልፍ ውጤት ተደርጎ ይታያል፡፡ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እና የአካባቢውን ህዝብ በቀጥታ የሚጠቅሙ አዳዲስ ስኬቶችን ለማስተዋወቅ የማያቋርጥ ጥረትን ያሳያል።
አዲስ ካፒታል እቃ ፋይናንስ በከተማዋ ኢኮኖሚ ውስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ወሳኝ አማራጭ የፋይናንስ አገልግሎት ሆኖ ያገለግላል። ተቋሙ በተለይ ለከተማው ወጣቶች እና ሴቶች የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት እና የውጭ ምንዛሪ ማመንጨት የሚችሉ እቃዎችን በማምረት ላይ ያተኩራል። ከዚህም በላይ ኩባንያው በስራ ዘርፎቹ ውስጥ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማስፋፋት በንቃት እየሰራ ነው።
ዘመናዊው ሕንፃ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማስተናገድ የተነደፈ ሲሆን ይህም ለባንክ፣ ለኢንሹራንስ እና ለቢሮ ቦታ ተስማሚ ያደርገዋል። ለሠራተኞቹ ውጤታማ እና ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲኖር ለማድረግ ተቋሙ እንደ የሕፃናት እንክብካቤ ማዕከል፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የጂምናዚየም አካባቢ እና ዘመናዊ ካፌቴሪያዎች ያሉ ሁሉን አቀፍ መገልገያዎችን ያካትታል።
ከንቲባ አዳነችሥነ ሥርዓቱን ሲዘጉ ፕሮጀክቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ለተሳተፉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
„ለዚህ ስኬት ያለመታከት ለሠሩት የቦርድ አባላት፣ ለአመራሮች፣ ለሠራተኞች፣ ለኮንትራክተሩ እና ለአማካሪው በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እና የጋራ ደስታችንን መግለጽ እፈልጋለሁ“ ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል። „እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክም!“ ብለዋል።
አቶ መሳይ እንሴኔ
የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር
የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ ምርትና ምርታማነት በመጨመር መሆኑን እና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የፋይናንስ ተቋማት በተለይ የሊዝ ኩባንያዎች አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሚሆን በመገንዘብ በሃገር ደረጃ ተቋቋመው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ በዚህም ኢንተርፕራይዞች ለሚያመርቱት ምርት በጥራትም ሆነ በገበያ ተወዳደሪነት መሻሻልና የማምረቻ መሳሪያ ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ለማኑፋክቸሪንግ ኮንስትራክሽን ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ እና አገልግሎት ኢንዱስትሪን በማስፋፋት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበርም አላማ አድርጎ የተነሳው በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ ዕውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክንያት መሳራት ላልቻሉ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ዕቃ ቅድመ ሁኔታ በሟሟላት የፋይናንስ እጥረታቸውን መቅረፍ ነው፡፡
ኩባንያው ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተመራቂዎች ፣ ለአዲስ ስራ ጀማሪዎችና ለሴት ስራ ፈጣሪዎቸ፣ ለተመረጡ ስኬታማ የንግድ ተቋማት እሴት የሚጨምር እና ተደራሽ የሆነ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብ የማምረቻ እና የኢንዱስትሪ ዘርፉን መደገፍ ላይ ትኩረት አድርጎ በመንቀሳቀስ ውጤታማ የካፒታል እቃ አቅርቦት ስርዓት የመገንባትን ተልእኮ በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
የጠቅላላ ጉባዔው አባላቱ በትናትናው ዕለት ኩባኒያው ባስገነባው አዲስ ህንጻ ላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ባተኮሩ አራት አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጽድቋል፡፡
ጉባዔው በተለይም የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ በሆኑት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራ አባይ ባቀረቡት የ2017 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን በማድመጥ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ማወቅ ተችሏል፡፡
በቀረበው ሪፖርት ላይ የጠቅላላ ጉባዔው አባል የሆኑት አቶ አዋሽ እንደገለጹት ከሆነ ተቋቋሙ ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ መሆኑንና ይህን መሰረት አድርጎ ደንበኞችን ለማርካት ከተደራሽነትም ሆነ ከአገልግሎት አንጻር በቀጣይ ብዙ ስለሚጠበቅበት ለመስራት ስትራተጂ አስቀምጦ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይም ትኩረት አድርጎ ሊሰራ ይገነባል፡፡
‘’የኩባኒያው የብድርና የኪራይ አመላለስ ጥሩ አፈጻጸም ላይ ነው’’ ያሉት የጠቅላላ ጉባዔው አባል የሆኑት አቶ አባተ ስጦታው የደንበኞች እርካታን በማወቅ ይበልጥ አገልግሎትን ለማሻሻል ዳሰሳ መደረግ አለበት፤ ከ IT ሲስተምም ጋር ተያይዞ ጊዜ ተወስዶ መሰራት እንዳለበት ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡
የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የ ኩባኒያው የጠቅላላ ጉባኤው አባል የሆኑ አቶ አብዱልቃድር በበኩላቸው ‘’ኩባኒያው በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ይህን ህንጻ ገንብቶ እዚህ ደረጃ ላይ ማድረሱና የፋይናንስ ዕጥረት ኖሮበትም ኢንተርፕራይዞችን በማስጠቀም በዚህ ቁመና መዝለቁ የሚበረታታ ነው’’ ብለዋል፡፡
የጠቅላላ ጌባዔ አባላቱ ባነስዋቸው የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ እና የኩባኒያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሳይ እንሴኔ ምላሾችን ሰጥተዋል፡፡
የጠቅላላ ጉባዔው አባላት የ2017 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፓርትና የውጭ ኦዲተር ሪፓርት በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
የኩባንያው ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ የማህበራዊ ተሳትፎ